“ቁጥር 7 ኢትዮጵያዊነት የሚበየንበት ክፍል ነው” – ፓስፖርት ለማግኘት የሚንገላቱ የትግራይ ተወላጆች

screenshot 2025 09 25 145113

“ሌባ አይደለሁም፣ ትክክለኛ ማስረጃዎች ይዤ፣ ምንም ሳላጠፋ ነው የሄድኩት። እንዲህ መዋሸት፣ ፀጉሬን ቀይሬ መሄድ፣ መንገላታት አያስፈልገኝም ነበር” ይላል ከትግራይ ተወላጅ ቤተሰቦች መገኘቱ ፓስፖርት ለማውጣት ፈተና ያሳየው ናሆም ሰለሞን*

የአዲስ አበባ ነዋሪው ናሆም፤ ከሁለት ወር መመላለስ እና እንግልት በኋላ ፓስፖርት ማግኘት የቻለው የእናት እና አባቱን የትውልድ ስፍራ በመቀየር “ደሴ እና ድሬዳዋ” ብሎ ከተናገረ በኋላ እንደሆ ያስረዳል።

ይህንንም ሲያደርግ በተደጋጋሚ የተመላለሰባቸው የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ኦፊሰሮች እንዳይለዩት ገጽታውን ቀይሮ መቅረቡን ይገልጻል።

“ፀጉሬን አፍሮ ነበር ወደላይ የማበጥረው፤ [ከአንድ ቀን በፊት] በሻምፖ አድርጌ በጣም ደምድሜው፣ በሹራብ ኮፍያ አድርጌ ነው ያሳደርኩት” ይላል፤ ደጋግሞ ካነጋገራቸው ኦፊሰሮች ራሱን ለመደበቅ የተጠቀመውን መንገድ ሲያስታውስ።

“አያቴ ልጅ እያለች ነው [ከትግራይ] አዲስ አበባ የመጣችው። ኖራ የሞተችው ጣልያን ሰፈር ነው። እናቴም እዚያው ነው የተወለደችው” ሲል እንግልት ያሳየው የአያቱ የትግራይ ተወላጅነት መሆኑን ይገልጻል። Read more

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *