
የኤርትራ መንግሥት የቀድሞ የሠራዊት አባላት ወደ የክፍሎቻቸው ለዳግም ሥልጠና እንዲመለሱ እና ሌሎችም ከአገር ለመውጣት የሚጠበቅባቸውን መስፈርቶች እንዳጠበቀ በኤርትራ ውስጥ እና በውጪ ሀገራት የሚገኙ የአገሪቱ ዜጎች ለቢቢሲ አረጋገጡ።
በዚህ መመሪያ መሠረት ከ60 ዓመት በታች የሚገኙ በኤርትራ ሠራዊት ውስጥ ያገለገሉ ዜጎች ተመዝግብው ወደ ማሠልጠኛ እንዲገቡ፤ እንዲሁም ከ50 ዓመት በታች የሆኑ ሰዎች ደግሞ ተገቢውን ፈቃድ ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ሳያገኙ ከአገር እንዳይወጡ ያዛል።
ቢቢሲ ትግርኛ ያነጋገራቸው የአሥመራ ከተማ ነዋሪዎች ይህ የኤርትራ መንግሥት ትዕዛዝ በይፋ የተገለጸ አለመሆኑን ተናግረዋል። ነዋሪዎቹ እንደሚያስረዱት ይህ ትዕዛዝ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ያወቁት ከአገር ለመውጣት እና የተለያዩ መንግሥታዊ አገልግሎቶችን ለማግኘት ወደ ቀበሌዎች በሄዱበት ወቅት በኃላፊዎች በተደረገላቸው ገለጻ ነው። Read more